አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 20፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ምሥራቅ ጉራጌ ዞን ርዕሰ መሥተዳድር እንዳሻው ጣሰው በተገኙበት የወጣቶች ተሳትፎና ተጠቃሚነት ላይ ያተኮረ መድረክ በቡኢ ከተማ እየተካሄደ ነው።
መድረኩ የዞኑን ወጣቶች ለአካባቢያቸው ሰላም፣ ልማት እና እድገት መረጋገጥ ያላቸውን ተሳትፎና ተጠቃሚነት ለማጎልበት ያለመ መሆኑ ተገልጿል፡፡
ወጣቶቹ በማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ዘርፎች ለሚያነሷቸው ጥያቄዎች ርዕሰ መሥተዳድሩ ምላሽ እንደሚሰጡ ኢዜአ ዘግቧል፡፡
በተለይ በምሥራቅ ጉራጌ ዞን ያሉትን የተፈጥሮ ጸጋዎች በማልማት የወጣቶችን ተጠቃሚነት በቅንጅት ለማረጋገጥ የሚያስችሉ ሥራዎችን ለመሥራት አቅጣጫ እንደሚቀመጥ ዘገባው አመላክቷል፡፡