አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 19፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ከፅናት ለኢትዮጵያ እና ከሰላም እና አንድነት ለኢትዮጵያ ማኅበራት የተሰባሰቡ አጀንዳዎችን ከማኅበራቱ ተወካዮች ተረከበ፡፡
ማኅበራቱ መቀመጫቸውን በሀገር ውስጥ እና በውጭ በማድረግ በተለያዩ ሀገራዊ ጉዳዮች ዘርፈ-ብዙ ተግባራትን አከናውነዋል መባሉን የኮሚኑ መረጃ አመላክቷል፡፡
በዛሬው ዕለትም በተወካዮቻቸው አማካኝነት ማኅበራቱ ሀገራዊ መግባባት ሊደረግባቸው ይገባል ብለው ያመኑባቸውን የምክክር አጀንዳዎችን ለኮሚሽኑ ማስረከባቸው ተገልጿል፡፡
በቀጣይም ከኮሚሽኑ ጋር በጋራ በመሥራት በኢትዮጵያ የሚካሄደውን የምክክር ሂደት ለመደገፍ ቁርጠኛ መሆናቸውን አረጋግጠዋል፡፡
የኮሚሽኑ ዋና ኮሚሽነር መስፍን አርዓያ (ፕ/ር) አጀንዳዎቹን በተረከቡበት ወቅት÷ የዳያስፖራው ማኅበረሰብ በተለያዩ መንገዶች አጀንዳውን በመስጠት በሀገራዊ ምክክሩ ሂደት ንቁ ተሳትፎ እንዲያደርግ ጥሪ አቅርበዋል፡፡