አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 19፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የሊባኖስ ታጣቂ ቡድን ሂዝቦላህ ናኢም ቃሲምን የቡድኑ መሪ አድርጎ መርጧል፡፡
ሂዝቦላህ የቡድኑ መሪ የነበረው ሃሰን ናስራላህ በቅርቡ በእስራኤል ጦር ጥቃት መገደሉን ተከትሎ ነው ናኢም ቃሲምን የቡድኑ መሪ አድርጎ የመረጠው፡፡
የ71 ዓመቱ ናኢም ቃሲም ከዚህ ቀደም በቡድኑ ውስጥ ለረጅም ዓመታት በተለያዩ የሃላፊነት ቦታዎች ላይ ማገልገሉን የሬውተርስ ዘገባ አመላክቷል፡፡
የሂዝቦላህ ታጣቂ ቡድንን ለረጅም ዓመታት ሲመሩ የነበሩት ሃሰን ናስራላህ ከአንድ ወር በፊት እስራኤል በቤሩት በፈጸመችው የአየር ጥቃት መገደሉ ይታወሳል፡፡
በተመሳሳይ ናስረላህን ይተካል ተብሎ ሲታሰብ የነበረው ሃሺም ሴፊየዴን ከሳምንታት በፊት በእስራኤል ጥቃት መገደሉ ይታወቃል፡፡