Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) በጌዴኦ ዞን የሚገኝ አዳሪ 2ኛ ደረጃ ት/ቤትን ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 19፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የትምህርት ሚኒስትር ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) በጌዴኦ ዞን የሚገኘውን ዳራሮ አዳሪ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ጎብኝተዋል፡፡

በጉብኝት መርሐ ግብሩ የዞኑ እና የትምህርት ቤቱ የሥራ ሃላፊዎች መሳተፋቸውን የዞኑ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

በተጨማሪም ሚኒስትሩ የዲላ አጠቃላይ ሆስፒታልን የሥራ እንቅስቃሴ ተዘዋውረው ተመልክተዋል።

ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) በቀጣይ በመልካም አስተዳደርና በትምህርት ጥራት ዙሪያ ከዲላ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንትና ሌሎች ከፍተኛ የሥራ ሃላፊዎች እንዲሁም መምህራንና የአስተዳደር ሰራተኞች ጋር እንሚወያዩም ተጠቁሟል፡፡

 

Exit mobile version