የሀገር ውስጥ ዜና

የሆስፒታሊቲ ኢንዱስትሪው ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ እንዲሆን አስቻይ ሁኔታ መዘርጋቱ ተገለጸ

By amele Demisew

October 29, 2024

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 19፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የሆስፒታሊቲ ኢንዱስትሪው ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ ተወዳዳሪ አገልግሎት እንዲያቀርብ መንግሥት አስቻይ ስልቶች መዘርጋቱን ቱሪዝም ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

የቱሪዝም ሚንስትር ሰላማዊት ካሳ ከሆቴል ፌዴሬሽኖች፣ ከቱሪዝም የሙያ ማኅበራት ኃላፊዎች እናተወካዮች ጋር በቅንጅት መሥራት በሚቻልበት ጉዳይ ላይ ተወያይተዋል፡፡

በዚሁ ወቅት የሆስፒታሊቲ ኢንዱስትሪው ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ ተወዳዳሪ አገልግሎት እንዲያቀርብ መንግሥት አስቻይ የማበረታቻ ስልቶች መዘርጋቱን ሚኒስትሯ ገልጸዋል፡፡

በዚህም በቅንጅት በመሥራት የአገልግሎት አሰጣጥን በማማሻሻል ዘርፉ የተጣለበትን ሀገራዊ ሚና እንዲያበረክት መሥራት እንደሚገባ ማሳሰባቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ አመላክቷል፡፡

የማኅበራቱ ተወካዮቹ በበኩላቸው ዘርፉ የሚጠበቅበትን እንዲያሳከ በቅርበት እና በተሻለ ትብብር እንደሚሠሩ አረጋግጠው÷ መንግሥት ለቱሪዝም ኢንዱስትሪው የሰጠውን ትኩረት አድንቀዋል፡፡