Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በኢትዮጵያ ሴቶች ያሉበት ደረጃ ላይ ያተኮረ የዳሰሳ ጥናት ይፋ ሆነ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 18፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያውያን ሴቶች ያሉበት ደረጃና ቅድሚያ ስለሚሰጧቸው ጉዳዮች ሁኔታ ላይ የተካሄደ ሀገር አቀፍ የዳሰሳ ጥናት ይፋ ተደርጓል።

ጥናቱን ላለፉት 2 ዓመታት የሴቶችና ማሕበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ የኢትዮጵያ ሴቶች ማህበራት ኔትወርክ፣ ኦክስፋም ኢትዮጵያ እና የአውሮፓ ህብረት ልዑካን በጋራ አከናውነውታል።

የጥናት ሰነዱን ይፋ ያደረጉት የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ/ር)÷የሥርዓተ-ፆታ እኩልነትን ለማስፈንና ሴቶችን ለማብቃት ምቹ ፖሊሲና ስትራቴጂ መነደፉን ገልፀዋል።

ይሁን እንጂ ከግማሽ በላይ ስለሚሆኑት ሴቶች እና ስለሴቶች ጉዳይ ያሉት መረጃዎች የተበታተኑ እና የተገደቡ መሆናቸውን አስረድተዋል፡፡

ሀገር አቀፍ የዳሰሳ ጥናቱ የኢትዮጵያን ሴቶች ሁኔታ እና ቅድሚያ የሚሰጧቸው ጉዳዮች በተመለከተ የተሟላ መረጃ ለመስጠት ትልቅ አስተዋፅኦ እንደሚኖረው ተናግረዋል ።

ጥናቱ ለፖሊሲ አውጪዎች፣ ለሥርዓተ-ፆታ ተሟጋቾች፣ ለመገናኛ ብዙኃን እና ለተመራማሪዎች አጋዥ መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡

የዳሰሳ ጥናቱ በ8 ክልሎች36 ሺህ 367 ሴቶችን ቃለ መጠይቅ በማድረግ የተከናወነ መሆኑን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡

Exit mobile version