Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በክልሉ የሚከሰቱ ሰብዓዊ ችግሮችን በራስ አቅም ለመሸፈን እየተሰራ ነው – አቶ አሻድሊ ሃሰን

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 18፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በተፈጥሮና ሰው ሰራሽ አደጋዎች የሚከሰቱ ሰብዓዊ ችግሮችን በራስ አቅም ለመሸፈን በትኩረት እየተሰራ መሆኑን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አሻድሊ ሃሰን ገለጹ፡፡

ርዕሰ መስተዳድሩ የክልሉን የአደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን የሥራ እንቅስቃሴ በጎበኙበት ወቅት እንዳሉት÷ እንደሀገር በተፈጥሮም ሆነ ሰው ሰራሽ  አደጋዎች የሚፈጠሩ ሰብዓዊ ችግሮችን በራስ አቅም ለመሸፈን በትኩረት እየተሰራ ነው፡፡

የቤኒሻንሻንጉል ጉሙዝ ክልልም በዚሁ ሀገራዊ አቅጣጫ መሰረት ያለውን ሰፊና ለም መሬት በአግባቡ ተጠቅሞ የምግብ ዋስትና ተልዕኮን ለማሳካት ወደ ሥራ መግባቱን ገልፀዋል፡፡

በዘንድሮው ዓመት የክልሉ አደጋ ሥጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ያከናዎናቸው ተግባራት አበረታች  መሆናቸውን ጠቁመው÷በቀጣይ የክልሉ መንግስት በሰፊው ወደ ሥራ ለመግባት የሚያግዙ ድጋፎች እንደሚያደርግ ተናግረዋል፡፡

የኮሚሽኑ ኮሚሽነር መሃመድ አብዱልአዚዝ በበኩላቸው÷በክልሉ የሰብዓዊ ድጋፍን በራስ አቅም ለመቻል በተከናወኑ ተግባራት ከ11 ሺህ 56 ሔክታር በላይ የእርሻ መሬትን በግብርና ምርት መሸፈን እንደተቻለ መናገራቸውን የክልሉ ግብርና ቢሮ መረጃ ያመላክታል፡፡

Exit mobile version