አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 18፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮ-ደቡብ አፍሪካ ቢዝነስ ፎረም በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው፡፡
በፎረሙ በሀገራቱ መካከል ያለውን የንግድና ኢንቨስትመንት ግንኙነት ይበልጥ ማጠናከር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ምክክር እንደሚደረግ ተገልጿል፡፡
በተጨማሪም በቀጣይ በትብብር ሊሰሩ በሚችሉባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት እንደሚካሄድ መጠቆሙን የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ም/ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡