Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ከወጪ ንግድ የሚገኘውን ገቢ ለማሳደግ በትኩረት እየተሰራ ነው – ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር)

 

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 18፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ)ከወጪ ንግድ የሚገኘውን ገቢ ለማሳደግ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) ገለፁ፡፡

የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አመራርና ሰራተኞች የ2017 ዓ.ም በጀት ዓመት የመጀመሪያውን ሩብ ዓመት እቅድ አፈፃፀም እየገመገሙ ነው፡፡

ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) በዚህ ወቅት÷በበጀት ዓመቱ 1ኛ ሩብ ዓመት ሚኒስቴር መ/ቤቱ ክትትል ከሚያደርግባቸው ምርቶች የወጪ ንግድ 1 ቢሊየን 508 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ገቢ መገኘቱን ገልጸዋል፡፡

ይህም ከባለፈው በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር የ700 ሚሊየን ዶላር ብልጫ እንዳለው መናገራቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

በንግድ ስርዓትና ላይሰንሲንግ ዘርፍ ከ900 ሺህ በላይ ኦንላይን የንግድ ምዝገባና ፈቃድ አገልግሎት መሰጠቱን ገልፀው ይህም ከባለፈው በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር የ450 ሺህ ብልጫ እንዳለው ገልፀዋል፡፡

የኑሮ ውድነትን ለመቀነስና ገበያውን ለማረጋጋት አማራጭ ገበያዎችን ከማስፋፋት አንፃርም በሩብ ዓመቱ 88 አዳዲስ የሰንበት ገበያዎች የተመቻቹ መሆኑንና በአጠቃላይ 1 ሺህ 334 የሰንበት ገበያዎች ተመቻችተው አገልግሎት እየሰጡ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

 

Exit mobile version