ስፓርት

4 ኢትዮጵያውያን አትሌቶች የዓመቱ ምርጥ አትሌት ዕጩ ውስጥ ተካተቱ

By Mikias Ayele

October 28, 2024

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 18፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያውያኑ አትሌቶች ዮሚፍ ቀጀልቻ፣ ታምራት ቶላ፣ ትዕግስት ከተማ እና ሱቱሜ አሰፋ የ2024 ከስታዲየም ውጭ የወንዶች የዓመቱ ምርጥ አትሌት ምርጫ ላይ በዕጩነት ተካተቱ፡፡

አትሌቶቹ በውድድር ዓመቱ በተለያዩ የጎዳና ላይ ውድድሮች ባስመዘገቡት ውጤት ነው ለዕጩነት መካተት የቻሉት።

በውድድር ዓመቱ አትሌት ታምራት ቶላ የኦሊምፒክ እና የበርሊን ማራቶንን ክብረ ወሰን በማሻሻል ጭምር ማሸነፉ ይታወሳል፡፡

እንዲሁም አትሌት ዮሚፍ ቀጀልቻ በቫሌንሺያ በተካሄደው የግማሽ ማራቶን ውድድር የዓለም ክብረ ወሰን በማስመዝገብ ማሸነፉ ይታወቃል፡፡

እንዲሁም በሴቶች አትሌት ትዕግስት ከተማ እና ሱቱሜ አሰፋ በዕጩነት መካተታቸውን የዓለም አትሌቲክስ መረጃ አመላክቷል፡፡