Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

108 አዲስ የኢንቨስትመንት ፈቃድ ተሰጥቷል- ኮሚሽኑ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 18፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በያዝነው የበጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት 108 አዲስ የኢንቨስትመንት ፈቃድ ለባለሃብቶች መሰጠቱን የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን አስታወቀ፡፡

ኮሚሽኑ የሩብ ዓመቱን ዕቅድ አፈጻጸም በገመገመበት ወቅት 108 አዲስ የኢንቨስትመንት ፈቃድ መሰጠቱ የተገለጸ ሲሆን÷ ፈቃድ የተሰጣቸውም የውጭ ባለሃብቶች፣ የውጭና የሀገር ውስጥ ባለሃብቶች በጥምርታ እና የሀገር ውስጥ ባለሃብቶች መሆናቸው ተብራርቷል፡፡

ለሀገር ውስጥ ባለሃብቶች ብቻ ተከልሎ የነበረው የንግድ ዘርፍ ለውጭ ባለ ሃብቶች በመከፈቱ 78 ባለሃብቶች ፍላጎት አሳይተው 24 ያህሉ ፕሮፖዛል ማቅረባቸውን እና ከዚህ ውስጥ የ20ዎቹ ጸድቆ የኢንቨስትመንት ፈቃድ በማውጣት ሂደት ላይ መሆናቸው ተገልጿል፡፡

ነባር የኢንዱስትሪ ፓርኮችን ወደ ልዩ ኢኮኖሚ ዞን የማሸጋገር ሥራ ተከናውኗል መባሉን የኮሚሽኑ መረጃ አመላክቷል፡፡

በሩብ ዓመቱ 131 ነጥብ 4 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ዋጋ ያላቸው ምርቶች ለውጪ ገበያ መቅረባቸውም ነው የተገለጸው፡፡

Exit mobile version