Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

125 ኢትዮጵያውያን ከሊባኖስ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 18፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በሊባኖስ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ 125 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በሊባኖስ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ለመመለስ ከባለድርሻ አካላት ጋር ትኩረት ሰጥቶ እየተንቀሳቀሰ እንደሚገኝ ገልጿል፡፡

በዚህም ሚኒስቴሩ ቤይሩት ከሚገኘው የኢትዮጵያ ቆንስላ ጄኔራል ጽ/ቤት ጋር በመሆን በቀጣይም ሌሎች ለችግር ተጋላጭ የሆኑ ዜጎችን ወደ ሀገራቸው ለመመለስ አስፈላጊውን ጥረት እያደረገ መሆኑን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡

Exit mobile version