Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

አርሰናል እና ሊቨርፑል አቻ ተለያዩ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 17፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 9ኛ ሣምንት ጨዋታ በሜዳው ሊቨርፑልን ያስተናገደው አርሰናል 2 አቻ ተለያይቷል።
1 ሠዓት ከ30 ላይ በተካሄደው ጨዋታ፥ ቡካዮ ሳካ እና ሚኬል ሜሪኖ የመድፈኞቹን ግቦች አስቆጥረዋል።
ቨርጅል ቫን ዳይክ እና ሞሐመድ ሳላህ ደግሞ የሊቨርፑልን ጎሎች ከመረብ አሳርፈዋል።
በተመሳሳይ 11 ሠዓት ላይ በተደረጉ ጨዋታዎች፥ ቼልሲ ኒውካስልን 2 ለ 1፣ ክሪስታል ፓላስ ቶተንሃምን 1 ለ 0 ረትተዋል።
እንዲሁም ዌስትሃም ማንቼስተር ዩናይትድን 2 ለ 1 አሸንፏል።
Exit mobile version