Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የአሰልጣኝ አስራት ሃይሌ ስርዓተ-ቀብር ተፈፀመ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 17፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የአሰልጣኝ አስራት ሃይሌ የቀብር ስነ ስርዓት በዛሬው ዕለት በጴጥሮስ ወጳውሎስ መካነ መቃብር ተፈፅሟል፡፡

በኢትዮጵያ እግር ኳስ ታሪክ በተጫዋችነትና አሰልጣኝነት ለረጅም ዓመታት ያገለገለው አስራት ሃይሌ (ጎራዴው) ከትናንት በስቲያ ከዚህ ዓለም በሞት መለየቱ ይታወቃል፡፡

ዛሬ ረፋድ ላይም ወዳጅ ዘመዶቹና አድናቂዎቹ በተገኙበት በአዲስ አበባ ስታዲየም የሽኝት መርሐ ግብር ተካሂዷል፡፡

አሰልጣኝ አስራት ሃይሌ ውጣ ውረድን አልፎ በርካታ ድልን በተጫዋችነትና በአሰልጣኝነት የተቀዳጀ ጠንካራ የስፖርት ሰው የነበረ ሲሆን÷ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንን ጨምሮ የተለያዩ ክለቦችን በተጫዋችነትና በአሰልጣኝነት በማገልገል በርካታ ዋንጫ አንስቷል።

አሰልጣኝ አስራት የስምንት ልጆች አባት ነበር።

Exit mobile version