አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 17፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የአጀንዳ ማሰባሰብና የምክክር ምዕራፍ በነገው ዕለት እንደሚጀምር አስታውቋል።
ኮሚሽኑ በወላይታ ሶዶ ከተማ የአጀንዳ ማሰባሰብ ስራውን ነገ እንደሚጀምር ኮሚሽነር ዮናስ አዳዬ (ዶ/ር) ናቸው ያስታወቁት፡፡
በአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደቱ በክልሉ ከሚገኙ ሁሉም ዞኖች የተውጣጡ ተወካዮች በየአካባቢያቸው ያለውን አጀንዳ በውይይት ያሰባሰቡ ሲሆን÷ ከነገ ጀምሮ በሚኖረው መድረክ ደግሞ እንደሚያቀርቡ ተናግረዋል፡፡
በሂደቱም የሐይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የሲቪል ተቋማት፣ ተጽዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦችን ጨምሮ ከ1 ሺህ 950 እስከ 2 ሺህ ሰዎች እንደሚሳተፉ ተገልጿል።
በዘመን በየነ