የሀገር ውስጥ ዜና

ካንሰርን ለመከላከል ስትራቴጂ ተነድፎ እየተሠራ መሆኑ ተመላከተ

By Mikias Ayele

October 27, 2024

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 17፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በሀገር አቀፍ ደረጃ ካንሰርን ለመከላከል የሚያስችል ስትራቴጂ ተነድፎ እየተሠራ መሆኑን የጤና ሚኒስትር ዶክተር መቅደስ ዳባ አስታወቁ፡፡

ዓለም ፍሬ ፒንክ ሃውስ ካንሰር ፋውንዴሽን የበጎ አድራጎት ድርጅት ዓመታዊ የጡት ካንሰር ወርን ምክንያት በማድረግ “ብርታትሽ ብርታቴ” በሚል መሪ ሐሳብ የእግር ጉዞ አካሂዷል።

ዶክተር መቅደስ በዚሁ ወቅት የካንሰር ህሙማንን መደገፍ እንደሚገባ ገልፀው÷ ካንሰርን ለመከላከልና አክሞ ለማዳን የሚያስችል ስትራቴጂ ተነድፎ እየተሠራ ነው ማለታቸው የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ አመላክቷል፡፡

የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ/ር) በበኩላቸው÷ በግንዛቤ እጥረትና መዘናጋት በጡትና የማህፀን በር ጫፍ ካንሰር በርካታ ሴቶች እንደሚጠቁ አስረድተዋል፡፡

ካንሰር በጊዜ ከተደረሰበትና ሕክምና ከተደረገለት በቀላሉ ስለሚድን ሴቶች በየጊዜው የካንሰር ቅድመ ምርመራ የማድረግ ልምዳቸውን እንዲያዳብሩ አስገንዝበዋል፡፡