አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 17፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በኮምቦልቻ ከተማ የሚገኙ የብልፅግና ፓርቲ ደጋፊዎች የሰላም የእግር የእግር ጉዞ አድርገዋል፡፡
የኮምቦልቻ ከተማ ከንቲባ ሙሐመድ አሚን በዚሁ ወቅት ባደረጉት ንግግር÷ ከተማዋ በሰላምና በልማት ጎዳና ላይ እንደምትገኝ ገልጸዋል፡፡
ከልማት የሚገኘውን ጥቅም ዘላቂ ለማድረግም ማኅበረሰቡ ሰላሙን አስጠብቆ መቀጠል እንዳለበት አስገንዝበዋል፡፡
የኮምቦልቻ ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ሙሉጌታ አቢ በበኩላቸው÷ መንግሥት ከተማዋን ሰላም ለማድረግ የተለያዩ አደረጃጀቶችን በመጠቀም ማሕበረሰቡ ሰላሙን እንዲጠብቅ እየሠራ መሆኑን አንስተዋል።
ሰላም ለልማት በመሆኑ ሁሉም ለሰላም ሊቆም ይገባል ያሉት ኃላፊው÷ መንግሥት ሰላምን ለማስጠበቅ እየሠራ ያለውን ተግባር እንደሚያስቀጥልም ገልጸዋል።
ከድር መሐመድ