አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 17፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማዕከል ኃላፊ እና በብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አደም ፋራህ የተመራ ከፍተኛ ልዑክ ቻይና ቤጂንግ ገባ፡፡
ልዑኩ ቤጂንግ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርስም በቻይና ኮሙኒስት ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮችና በቻይና የኢትዮጵያ አምባሳደር ተፈራ ደርበው አቀባበል ተደርጎለታል፡፡
ልዑኩ ወደ ቻይና ያቀናው በዋናነት የፓርቲ ለፓርቲ ግንኙነትን ለማጠናከር መሆኑን የብልጽግና ፓርቲ መረጃ አመላክቷል፡፡
የልዑካን ቡድኑ በቆይታውም የሁለትዮሽ ውይይቶች፣ የተሞክሮ ልውውጦች እና የመስክ ጉብኝቶች እንደሚያደርግ ይጠበቃል ተብሏል፡፡
በተጨማሪም ልዑኩ በቀጣይ ሊኖሩ ስለሚችሉ ስትራቴጂያዊ ጉዳዮች እና የትብብር መስኮች መለየት የሚያስችል ውይይት እንደሚያደርግ ተጠቁሟል፡፡