Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የአርብቶ አደሩን ምርታማነትን ለማሳደግ የተጀመሩ ስራዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ – ር/መስተዳድር አለሚቱ ኡሞድ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 16፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በክልሉ የአርብቶ አደሩን ምርታማነት ለማሳደግ የተጀመሩ ስራዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ ሲሉ የጋምቤላ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አለሚቱ ኡሞድ ገለጹ፡፡

የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አለሚቱ ኡሞድና ሌሎች የክልሉ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች በክልሉ በአቦቦና በጎግ ወረዳ እየተከናወነ ያለን የሩዝ ሰብል ልማትና ሌሎች የልማት ስራዎች ጎብኝተዋል፡፡

ርዕሰ መስተዳድር አለሚቱ ኡሞድ በዚሁ ወቅት ÷ በክልሉ አዳዲስ የግብርና ምርት ዓይነቶችን በማስፋፋት የዘርፉን ምርታማነት ለማሳደግ በትኩረት እየተሰራ ነው ብለዋል።

በክልሉ ያሉትን ዕድሎች በመጠቀም ውጤታማ ለመሆን በዘርፉ የተሰማሩ አካላት ቅንጅታዊ አሰራር መጠናከር እንደሚኖርበትም ገልፀዋል።

ክልሉ በግብርናው ዘርፍ ያለውን አቅም ወደ ልማት በመቀየር ምርትን በብዛትና በጥራት ለማምረት ጥረት እያደረገ መሆኑን ተናግረዋል።

በሩዝ ልማቱ የተገኘው ተሞክሮ የሚበረታታ መሆኑን የጠቆሙት ርዕሰ መስተዳድሯ ÷ ክልሉ ለሩዝ ልማት ምቹ መሆኑን በምልከታው አረጋግጫለሁ ማለታቸውን ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

Exit mobile version