ስፓርት

አሰልጣኝ አስራት ሃይሌ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ

By Melaku Gedif

October 25, 2024

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 15፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ እግር ኳስ ታሪክ በተጫዋችነትና አሰልጣኝነት ለረጅም ዓመታት ያገለገለው አስራት ሃይሌ (ጎራዴው) ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ።

አሰልጣኝ አስራት ሃይሌ ባደረበት ህመም በህክምና ሲረዳ ቆይቶ ማረፉ ተሰምቷል።

አሰልጣኝ አስራት ሃይሌ ውጣ ውረድን አልፎ በርካታ ድልን በተጫዋችነትና በአሰልጣኝነት የተቀዳጀ ጠንካራ የስፖርት ሰው የነበረ ሲሆን፤ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንን ጨምሮ የተለያዩ ክለቦችን በተጫዋችነትና በአሰልጣኝነት በማገልገል በርካታ ዋንጫ አንስቷል።

አሰልጣኝ አስራት የስምንት ልጆች አባት ነበር።