Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ኢትዮጵያና ቻይና ግንኙነታቸውን በማጎልበት ለጋራ ተጠቃሚነት ሊሠሩ ይገባል – ተመራማሪዎች

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 15፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ እና ቻይና ታሪካዊ ግንኙነታቸውን በይበልጥ በማጠናከር ለጋራ ተጠቃሚነት ሊሠሩ እንደሚገባ የአፍሪካ ቻይና ጥናት ተመራማሪዎች አመላከቱ፡፡

የኢትዮጵያና ቻይና ግንኙነት በአክሱም ሥረወ-መንግሥት መጀመሩን እና ከ2 ሺህ ዓመታት በላይ ማስቆጠሩን በዤጂያንግ ኖርማል ዩኒቨርሲቲ የአፍሪካ ጥናቶች ተመራማሪ ዮሮ ዲያሎ (ፕ/ር) ገልጸዋል፡፡

ይህ ዘመናትን ያስቆጠረ ግንኙነት አሁንም ተጠናክሮ መቀጠሉን አንስተው÷ ለአብነትም በመሠረተ-ልማት፣ ትምህርት እና ኢንቨስትመንት ዘርፎች ውጤታማ ሥራ መከናወኑን አብራርተዋል፡፡

በዚሁ ዩኒቨርሲቲ የባህልና ኪነ-ጥበብ ተመራማሪ የሆኑት ታይሊን ሮድሪጎ በበኩላቸው÷ ታሪካዊውን ግንኙነት ለማስቀጠል የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነቶችን በይበልጥ ማጠናከር እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡

አፍሪካና ቻይና በደቡብ ደቡብ ግንኙነታቸው ችግሮቻቸውን በጋራ መፍታትና ትስስራቸውን ሁሉን አቀፍ ማድረግ እንደሚገባቸውም መክረዋል፡፡

በአፈወርቅ እያዩ

 

Exit mobile version