አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 15፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ሲቪል ሰርቫንቱ የሕዝብ እንግልትን የሚያስቀር ምቹ አገልግሎት የማቅረብ ኃላፊነት እንዳለበት የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር እንዳሻው ጣሰው አስገነዘቡ፡፡
ርዕሰ መሥተዳድሩ በተገኙበት የክልሉ ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ዘርፍ የምክክር መድረክ ተካሂዷል፡፡
በዚሁ ወቅት አቶ እንዳሻው ሲቪል ሰርቫንቱ የሕዝብ እንግልትን የሚያስቀር ምቹ እና ቀላል አገልግሎትን የማቅረብ ኃላፊነት እንዳለበት አስገንዝበዋል፡፡
በቅንነት ሕዝቡን ለማገልገል ዝግጁ መሆን እንደሚገባ ማሳሰባቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ መረጃ አመላክቷል፡፡
የሲቪል ሰርቪስ ሪፎርሙን አጠናክሮ በመያዝ በተለይም አስተሳሰብና አመለካከት ላይ ማተኮር እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡
መዋቅሩም በአመራሩም ሆነ በባለሙያው ተቀራራቢ አፈጻጸም እንዲመዘገብ ማድረግ ይኖርበታል ነው ያሉት፡፡