Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ኢትዮጵያ ለኮፕ 29 የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ ውጤታማነት ቅድመ ዝግጅት እያደረገች ነው

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 15፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ ለኮፕ 29 የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ ውጤታማነት ቅድመ ዝግጅት እያደረገች መሆኑን የፕላንና ልማት ሚኒስትር ፍጹም አሰፋ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡

በአዘርባጃን ባኮ ከሚካሄደው የኮፕ 29 የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ አስቀድሞ ኢትዮጵያ በሁነቱ ቅድሚያ በምትሰጣቸው እና በምትጠብቃቸው ውጤቶች ላይ ከአጋር እና ባለድርሻ አካላት ጋር እየመከረች ነው።

የፕላንና ልማት ሚኒስትሯ ፍጹም አሰፋ (ዶ/ር) በዚህ ወቅት ÷ከሁነቱ አስቀድሞ የአየር ንብረት ሳምንት እና ግንባር ቀደም ለህፃናት የአየር ንብረት ገጽታ ትንተና ጥናት በማቅረብ ኢትዮጵያ በሁነቱ ቅድሚያ በምትሰጣቸው ጉዳዮችላይ ውይይቱ እይተካሄደ እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡

የአየርንብረት ለውጥ የዓለም ስጋት መሆኑን ያነሱት ሚኒስትሯ ችግሩን በጋራ ለመከላከል ኢትዮጵያ ሁሉንም ባለድርሻዎች ባሳተፈ መልኩ እየሰራች መሆኑንም አንስተዋል።

የአለም አቀፉ ህጻናት አድን ድርጅት የኢትዮጵያ ተወካይ አቡበከር ካምፖ(ዶ/ር) በበኩላቸው ÷የአየር ንብረት ተጽዕኖን በመከላከል እና በመቋቋም ረገድ ኢትዮጵያ በርካታ ስራዎችን እያከናወነች ቢሆንም የህጻናት ግንዛቤ ማስጨበጥ ላይም የበለጠ መስራት እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

በይስማው አደራው

Exit mobile version