ስፓርት

በፕሪሚየር ሊጉ  መቐለ 70 እንደርታ ድሬዳዋ ከተማን አሸነፈ

By Shambel Mihret

October 24, 2024

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 14፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ)በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መቐለ 70 እንደርታ ድሬዳዋ ከተማን 3 ለ 2 አሸንፏል፡፡

በፕሪሚየር ሊጉ 5ተኛ ሳምንት መርሐ ግብር በድሬዳዋ ስታዲየም ቀን 10 ሰዓት ላይ መቐለ 70 እንደርታ እናከድሬዳዋ ከተማ ጨዋታቸውን አድርገዋል፡፡

የመቐለ 70 እንደርታ የማሸነፊያ ሁለት ጎሎችን ያሬድ ብርሃኑ ሲያስቆጥር አሸናፊ ሐፍቱ 3ተኛዋን ግብ ከመረብ ላይ አሳርፏል፡፡

አሥራት ቱንጆ እና መሐመድኑር ናስር ደግሞ የድሬዳዋ ከተማን ከሽንፈት ያልታደጉን ሁለት ግቦችን አስቆጥረዋል፡፡