የሀገር ውስጥ ዜና

በኢትዮጵያና በጀርመን መካከል ያለውን ግንኙነት ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ የጀርመን መንግሥት ድጋፍ እንደሚያደርግ አስታወቀ

By Feven Bishaw

October 24, 2024

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 14፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በጀርመን የኢትዮጵያ አምባሳደር እስክንድር ይርጋ የሹመት ደብዳቤያቸውን ለጀርመን ፕሬዚዳንት ፍራንክ-ዋልተር ሽታይንማየር አቅርበዋል።

አምባሳደር እስክንድር÷ በሚሲዮኑ በሚኖራቸው ቆይታ ከምዕተ-ዓመት በላይ ያስቆጠረውን የኢትዮጵያ እና የጀርመን ግንኙነት እንዲሁም በተለያዩ መስኮች ያለውን ትብብር ይበልጥ ለማጠናከር ትኩረት ሰጥተው እንደሚሰሩ ተናግረዋል።

በስራ ዘመናቸው ቅድሚያ ሰጥተው የሚሰሩባቸውን መስኮች በመጠቆም ለስኬታማነቱ የጀርመን መንግስትን ድጋፍ መጠየቃቸውን የኤምባሲው መረጃ ያመላክታል፡፡

ፕሬዚዳንት ፍራንክ-ዋልተር በበኩላቸው÷ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ግንኙነት ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ የጀርመን መንግሥት ድጋፍ እንደማይለያቸው ለአምባሳደሩ አረጋግጠዋል።