Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በመዲናዋ የትራፊክ መጨናነቅን ለመቀነስ የሚያግዝ ቴክኖሎጂ ይፋ ሆነ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 14፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ የሚስተዋለውን የትራፊክ መጨናነቅ ለመቀነስ የሚያግዝ አዲስ ቴክኖሎጂ ይፋ ሆኗል፡፡

የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር የስራ ኃላፊዎች ከጉባ ቴክኖሎጂ የስራ ኃላፊዎች ቴክኖሎጂውን በተመለከተ ውይይት አድርገዋል፡፡

በውይይታቸውም የትራፊክ ቁጥጥርን ለማገዝ በጉባ ቴክኖሎጂ አማካይነት የበለፀገው ቴክኖሎጂ ተገምግሟል።

የትራንስፖርትና ሎጅሰቲክስ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ እንዳመላከተው፤ አዲሱ ቴክኖሎጂ ተግባራዊ ሲደረግ በከተማው የትራፊክ መጨናነቅ በሚታይባቸው መንገዶች ከሰው ንኪኪ ነጻ የሆነ መረጃ መቀበል ይቻላል።

በዚህም መረጃውን በግብዓትነት በመጠቀምም አማራጭ መንገዶችን በማመላከት የትራፊክ መጨናነቅን ለመቀነስ እንደሚያስችል ተገልጿል፡፡

Exit mobile version