የሀገር ውስጥ ዜና

የ2017 የተማሪዎች የዩኒቨርሲቲ ምደባ ይፋ ሆነ

By Shambel Mihret

October 24, 2024

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 14፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የ2017 ዓ.ም የተማሪዎች የዩኒቨርሲቲ ምደባ ይፋ መሆኑን የትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

ሚኒስቴሩ እንደገለጸው÷በ2016 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ ሃገር አቀፍ ፈተና ወስደው በመደበኛው ፕሮግራም ለትምህርት ሚኒስቴር ተጠሪ በሆኑ የመንግስት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ትምህርታቸውን ለመከታተል የሚያስችል ማለፊያ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች የተቋም ምደባቸውን ከአሁን ሰዓት ጀምሮ እንደሚከተለው በተዘረዘሩት አማራጮች ማየት ይችላሉ፡፡

በዚህም ተማሪዎች የመንግስት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በሚያስተላልፉት ጥሪ መሰረት ምዝገባ እንዲከታተሉ መልዕክት ያስተላለፈው ሚኒስቴሩ የተቋም ይቀየርልኝ ጥያቄ የማያስተናግድ መሆኑንም ገልጿል፡፡