የሀገር ውስጥ ዜና

አስጎብኚ ማህበራት የሚያጋጥማቸውን ችግሮች ለመፍታት እንደሚሰራ ተገለጸ

By Shambel Mihret

October 24, 2024

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 14፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) አስጎብኚ ማህበራት ከአሰራር ጋር በተያያዘ የሚያጋጥማቸውን ችግሮች ለመፍታት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር እንደሚሰራ የቱሪዝም ሚኒስቴር ገለጸ፡፡

የቱሪዝም ሚኒስትሯ ሰላማዊት ካሳ ከአስጎብኚ ማህበራት ኃላፊዎች ጋር በጋራ መስራት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል፡፡

በዚሁ ወቅት ሰላማዊት ካሳ÷ከአሰራር ጋር በተያያዘ የተነሱ ጉዳዮችን በተቋማቸው መከናወን ያለባቸውን ተግባራት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመነጋገር መፍትሄ እንደሚሰጥ ገልፀዋል፡፡

የዘርፉ ባለድርሻ አካላት የበኩላቸውን አስተዋፅዖ እንዲያበረክቱም መልዕክት ማስተላለፋቸውን ከቱሪዝም ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡

የማህበራቱ ተወካዮቹ በበኩላቸው÷መንግሥት ቱሪዝም በኢኮኖሚ ዘርፍ ውስጥ እንዲካተት ከማድረግ ባሻገር አዳዲስ የቱሪስት መስህብ ስፍራዎችን በማልማት እያከናወነ ያለው ተግባር ለዘርፉ የሰጠውን ትኩረት የሚያሳይ ነው ብለዋል፡፡

በዘርፉ ያሉትን የቅንጅታዊ አሰራር ውስንነት፣ በመስህብ ስፍራዎች አካባቢ የሚስተዋሉ ህገ ወጥ እንቅስቃሴዎች እና ከአገልግሎት አሰጣጥ መጓደል ጋር በተያያዘ ያሉ ችግሮችን ጠቅሰዋል፡፡