Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

አቶ ሽመልስ አብዲሳ በጅማ ዞን የልማት ስራዎችን ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 14፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ እና ሌሎች የክልሉ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች በጅማ ዞን ጎማ ወረዳ የተለያዩ የልማት ስራዎችን ጎብኝተዋል።

በአቶ ሽመልስ አብዲሳ የተመራው የሥራ ኃላፊዎች ቡድን ሰሞኑን በኢሉአባቦር እና በቡኖ በደሌ ዞኖች የተለያዩ የልማት ስራዎችን ተመልክቷል።

በዞኖቹ በነበራቸው የልማት ስራዎች ጉብኝት ቆይታም የክልሉ መንግስት የተገበራቸው የግብርና ልማት ኢንሼቲቮች ተስፋ ሰጪ መሆናቸው ተገልጿል።

ከግብርና ልማት ኢንሼቲቮች መካከል የሻይ ቅጠል፣ የሩዝ፣ የቡና፣ የማር እና የአትክልትና ፍራፍሬ ልማት በተሻለ መልኩ እየተከናወነ መሆኑ መገለጹን የዘገበው ኢዜአ ነው።

በዛሬው ዕለትም አቶ ሽመልስ እና የክልሉ የስራ ኃላፊዎች በጅማ ዞን ጎማ ወረዳ የተለያዩ የግብርና ልማት ስራዎችን ጎብኝተዋል።

Exit mobile version