Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ባለፉት ሦስት ወራት ከ1 ነጥብ5 ቢሊየን ዶላር በላይ ገቢ ተገኘ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 14፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ባለፉት ሦስት ወራት ከ1ነጥብ 5 ቢሊየን ዶላር በላይ ገቢ መገኘቱን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ(ዶ/ር) ገለጹ፡፡

ካሳሁን ጎፌ(ዶ/ር) በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መረጃ÷ ዛሬ የ2017 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት የወጪ ንግድ አፈጻጸም ከላኪዎች ጋር መገምገሙን ገልጸዋል።

አፈጻጸሙ በምርት ጭማሪም ሆነ በውጭ ምንዛሪ ዕድገት ካለፈው በጀት ዓመት አፈጻጸም ጋር ሲነጻጸር ከፍተኛ ለውጥ ማሳየቱን አንስተዋል፡፡

በዚህም ባለፉት ሦስት ወራት ከ1 ነጥብ 5 ቢሊየን ዶላር በላይ ገቢ መገኘቱን ጠቁመዋል፡፡

ይህም የእቅዱን 132 በመቶ ሲሆን ፥ ከአምና ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር ከ700 ሚሊየን ዶላር በላይ ጭማሪ እንዳለውም ነው ሚኒስትሩ የገለጹት፡፡

በዓመቱ ቀሪ ወራት ዕቅድ አፈጻጸሙን በማላቅ ኢኮኖሚው የሚፈልገውን የውጭ ምንዛሪ ግኝት ለማሳደግ ከዘርፉ ተዋናዮች ጋራ መግባባት ላይ መደረሱንም ጠቁመዋል።

Exit mobile version