የሀገር ውስጥ ዜና

የካፍ ልዑክ የዓድዋ ድል መታሰቢያን ጎበኘ

By amele Demisew

October 24, 2024

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 14፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) ልዑክ አባላት የዓድዋ ድል መታሰቢያን ጎብኝተዋል፡፡

በጉብኝታቸው ወቅት ልዑካኑ በሰጡት አስተያየት ÷የዓድዋ ድል ታሪክ በአፍሪካ ስርዓተ ትምህርት ውስጥ ሊካተት ይገባል ብለዋል፡፡

እንዲሁም በአፍሪካ የሚገኙ ታዳጊ ህፃናት እና ወጣቶች የነፃነት እና የሰው ልጆች እኩልነት ፈር ቀዳጅ የሆነችውን ኢትዮጵያን እና መታሰቢያውን እንዲጎበኙ ጥረት ሊደረግ ይገባል ማለታቸውን ከመታሰቢያ ሙዚየሙ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡