የሀገር ውስጥ ዜና

በሁለቱ ሀገሮቻችን ታሪካዊ ቁርኝት ላይ የተመሠረተው የሁለትዮሽ ግንኙነታችን እያደገ ቀጥሏል – ጠ/ሚ ዐቢይ(ዶ/ር)

By Feven Bishaw

October 24, 2024

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 14፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ እና ሩሲያ ታሪካዊ ቁርኝት ላይ የተመሠረተው የሁለትዮሽ ግንኙነት እያደገ መቀጠሉን ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ገለፁ፡፡

ኢትዮጵያ እና ሩሲያ በሁለትዮሽ መድረክ ውይይት አካሂደዋል፡፡

ይህንን ተከትሎ ጠ/ሚ ዐቢይ(ዶ/ር) በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ÷”በሁለትዮሽ መድረካችን ወቅት ላደረግነው ጥልቅ ውይይት ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲንን አመሰግናለሁ” ብለዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሁለቱ ሀገራት ታሪካዊ ቁርኝት ላይ የተመሠረተው የሁለትዮሽ ግንኙነት እያደገ መቀጠሉንም አመላክተዋል፡፡

በተጨማሪም የጋራ የሆነው የብሪክስ መድረክ ሰፋ ላለ የኢኮኖሚ ትብብር እንድንሰራ በር ከፍቶልናል ነው ያሉት ጠ/ሚ ዐቢይ(ዶ/ር)፡፡