Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የኢትዮጵያና ቻይና የቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ትብብር ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 13፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያና ቻይና በቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ያላቸውን ትብብር ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ እንደሚሠሩ ተገልጿል፡፡

የሥራና ክኅሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል ከቻይና የትምህርት ምክትል ሚኒስትር እና የቻይና ኮሙኒስት ፓርቲ ተወካይ ው ያን ጋር ተወያይተዋል።

ውይይቱ በትምህርትና ሥልጠናው ዘርፍ ያለውን የሁለቱን ሀገራት ስትራቴጂያዊ ግንኙነት ወደ ላቀ ደረጃ የሚያሸጋግር መሆኑን ሚኒስትሯ ገልጸዋል።

በኢትዮጵያ ብቸኛው የቴክኒክና ሙያ ልኅቀት ማዕከል ሆኖ እያገለገለ ያለው የቴክኒክና ሙያ ኢንስቲትዩት በቻይና መንግስት ድጋፍ መሰራቱንም አስረድተዋል፡፡

ው ያን በበኩላቸው ኢትዮጵያ በዘርፉ የጀመረችውን ሪፎርም አድንቀው በሁለቱ ሀገራት መካከል በቴክኒክና ሙያ ዘርፍ የነበረውን ግንኙነት ወደ ላቀ ደረጃ ለማሳደግ እንደሚሠሩ ማረጋገጣቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ አመላክቷል፡፡

በቀጣዮቹ ዓመታት ዘርፉን በቴክኖሎጂና በሰው ኃይል ማጠናከር እና ኢትዮጵያ የጀመረችውን የዘርፉን ሪፎርም መደገፍ የሚያስችሉ ተጨማሪ አዳዲስ የትብብር መስኮች ተለይተው ወደ ሥራ እንደሚገቡ ጠቁመዋል፡፡

Exit mobile version