Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ኢትዮጵያ እና ብሪታኒያ በደኅንነት ጉዳዮች ላይ በጋራ ለመሥራት ተስማሙ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 13፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ እና ብሪታኒያ በሰላም እና ደኅንነት ዘርፍ በትብብር ለመሥራት ተስማሙ፡፡

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ከብሪታኒያ ‘ሴክሬት ኢንተለጀንስ ሰርቪስ (MI6)’ ኃላፊ ሪቻርድ ሙር ጋር በአዲስ አበባ ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸውም በዓለም አቀፋዊ እና ቀጣናዊ የፀጥታ እና ደኅንነት ጉዳዮች ላይ መምከራቸውን አቶ ተመስገን በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ገልጸዋል፡፡

ኢትዮጵያ ከብሪታኒያ ጋር ላላት ጥልቅና የረጅም ጊዜ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ትልቅ ቦታ እንደምትሰጥም አስገንዝበዋል፡፡

ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ቀንድ ሰላም እና ደኅንነት እንደ ብሪታኒያ ካሉ አጋር ሀገራት ጋር በቅርበት እንደምትሠራ አረጋግጠዋል፡፡

በዚሁ መሠረት ሁለቱ ሀገራት በትብብር ለመሥራት ከስምምነት መድረሳቸውን  ነው አቶ ተመስገን ያስታወቁት፡፡

Exit mobile version