ስፓርት

መሳይ ተፈሪ የዋሊያዎቹ ጊዜያዊ አሰልጣኝ ሆኑ

By ዮሐንስ ደርበው

October 23, 2024

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 13፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ገብረ መድኅን ኃይሌን በመተካት መሳይ ተፈሪ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን (ዋሊያዎቹ) ጊዜያዊ ዋና አሰልጣኝ ሆኑ፡፡

በዚሁ መሠረት አሰልጣኝ መሳይ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በአፍሪካ ሀገራት ዋንጫ (ቻን) ማጣሪያ የሚያደርጋቸውን ጨዋታዎች እንዲመሩ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ውስኗል፡፡

አሰልጣኙ ላለፉት 12 ወራት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ምክትል አሰልጣኝ ሆነው ሲሠሩ መቆየታቸውን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን መረጃ አመላክቷል፡፡

ዋሊዎቹ ከኤርትራ ጋር የሚያደርጉትን ጨዋታ ጨምሮ የቻን ማጣሪያን በጊዜያዊ ዋና አሰልጣኝነት እንደሚመሩም ነው የተገለጸው፡፡