Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ኢትዮጵያ የመካከለኛው ምስራቅ ውጥረት እንዲረግብ ለማገዝ ዝግጁ ናት- ጠ/ሚ ዐቢይ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 13፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ የመካከለኛው ምስራቅ ውጥረቶች የሚረግቡበትን ሁኔታ ለማገዝ ዝግጁ መሆኗን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አረጋገጡ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዛሬ ጠዋት ከኢራን ፕሬዚዳንት መስዑድ ፔዥሺካን ጋር በሁለትዮሽ እና ቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ መወያየታቸውን በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ገልጸዋል፡፡

በውይይታቸው ወቅትም ኢትዮጵያ የመካከለኛው ምስራቅ ውጥረቶች የሚረግቡበትን ሁኔታ ለማገዝ ዝግጁ መሆኗን ገልጫለሁ ብለዋል፡፡

Exit mobile version