የሀገር ውስጥ ዜና

ኢትዮጵያ የተሳተፈችበት 16ኛው የብሪክስ ጉባዔ በዝግ ተካሄደ

By ዮሐንስ ደርበው

October 23, 2024

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 13፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) 16ኛው የብሪክስ ጉባዔ የተጠናከረ የባለ ብዙ ወገን ግንኙነት ለሚዛናዊ የዓለም ልማት እና ደኅንነት በሚል መሪ ሐሳብ በዝግ መካሄዱን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት አስታውቋል፡፡

በስብሰባው ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ንግግር አድርገዋል፡፡

ኢትዮጵያ በፈረንጆቹ 2023 ወደ ብሪክስ እንዲቀላቀሉ ከተጋበዙት ሀገራት መካከል መሆኗ ይታወቃል።

ይህን ተከትሎም ከ2024 ጀምሮ የአባልነቷ እንቅስቃሴ በይፋ መጀመሩን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት መረጃ አመላክቷል፡፡