የሀገር ውስጥ ዜና

ፖሊስ 25ኛ ዙር አዲስ ምልምል ኃይል ማሰልጠን ጀመረ

By ዮሐንስ ደርበው

October 23, 2024

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 13፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ለ25ኛ ዙር አዲስ የምልምል ኃይል ስልጠና መስጠት መጀመሩን አስታወቀ፡፡

ሰልጣኞቹ ከሁሉም የኢትዮጵያ ክልሎች የተወጣጡ መሆናቸውን የፌደራል ፖሊስ መረጃ አመላክቷል፡፡

ሥልጠናው የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስን የመፈፀም አቅም እና ተደራሽነት እንደሚያሳድግም ተጠቅሷል፡፡