አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 13፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) 16ኛው የብሪክስ ጉባዔ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት በሩሲያ ካዛን ከተማ እየተካሄደ ነው፡፡
በጉበዔው በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የተመራ ልዑካን ቡድን እየተሳተፈ ይገኛል፡
በተጨማሪም የተለያዩ ሀገራት መሪዎች፣ ርዕሰ ብሔሮች እንዲሁም ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች በጉባዔው ተሳትፈዋል፡፡
ለሦስት ቀናት በሚካሄደው ጉባዔ በአባል ሀገራት መካከል ያለውን የኢኮኖሚ እና የቴክኖሎጂ ትብብር ማጠናከር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ምክክር እንደሚደረግ ተጠቅሷል፡፡
ከጉባዔው ጎን ለጎንም የተለያዩ የሁለትዮሽ መድረኮች እንደሚካሄዱ ነው የተመላከተው፡፡