Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የ3ኛ ሳምንት የሻምፒየንስ ሊግ ጨዋታዎች ዛሬ ቀጥለው ይደረጋሉ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 13፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ሦስተኛ ሳምንት ሁለተኛ ቀን ጨዋታዎች ዛሬ ሲቀጥሉ ባርሴሎና እና ባየርን ሙኒክ የሚያደርጉት ፍልሚያ አጓጊ ሆኗል፡፡

ምሽት 1 ሠዓት ከ45 ቤርጋሞ ላይ የጣሊያኑ አታላንታ ከስኮትላንዱ ሴልቲክ እንዲሁም የፈረንሳዩ ብረስት ከጀርመኑ ባየር ሌቨርኩሰን ጨዋታቸውን ያደርጋሉ፡፡

በሌላ የጨዋታ መርሐ-ግብር ምሽት 4 ሠዓት ስታዲዮ ኦሎምፒኮ ላይ ባርሴሎና ከባየርን ሙኒክ የሚያደርጉት ጨዋታ ከፍተኛ ትኩረት አግኝቷል፡፡

በተመሳሳይ ምሽት 4 ሠዓት ላይ አትሌቲኮ ማድሪድ ከፈረንሳዩ ሊል፣ የፖርቹጋሉ ቤኔፊካ ከደቹ ፌይኖርድ፣ ማንቼስተር ሲቲ ከቼክ ሪፐብሊኩ ስፓርታ ፕራግ የጀርመኑ አር ቢ ሌይብዚግ ከሊቨርፑል ይጫወታሉ፡፡

በተጨማሪም የኦስትሪያው ሬድ ቡል ሳልዝበርግ ከክሮሽያው ዳይናሞ ዛግሬብ እና የስዊዘርላንዱ ያንግ ቦይስ ከኢንተርሚላን ምሽት 4 ሠዓት ላይ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ፡፡

ትናንት ምሽት በተደረጉ የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ጨዋታዎች÷ ሪያል ማድሪድ ቦሩሲያ ዶርትሙንድን 5 ለ 2፣ ኤሲሚላን ክለብ ብሩጅን 3 ለ 1፣ ሞናኮ ሬድ ስታር ቤልግሬድን 5 ለ 1፣ አርሰናል ሻክታር ዶኔስክን 1 ለ 0፣ አስቶንቪላ ቦሎኛን 2 ለ 0፣ ዢሮና ስሎቫን ብራቲስላቫን 2 ለ 0፣ ስቱትጋርት ጁቬንቱስን 1 ለ 0፣ ስፖርቲንግ ሊዝበን ስቱርም ግራዝን 2 ለ 0 ማሸነፍ ሲችሉ ፒኤስጂ እና ፒኤስቪ 1 ለ 1 ተለያይተዋል፡፡

Exit mobile version