የሀገር ውስጥ ዜና

ሆስፒታሉ 5 ነጥብ 8 ሚሊየን ብር ዋጋ ያለው የሕክምና ቁሳቁስ በድጋፍ አገኘ

By ዮሐንስ ደርበው

October 22, 2024

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 12፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) አለርት ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ለኢትዮጵያ ፖሊስ ሆስፒታል 5 ነጥብ 8 ሚሊየን ብር የሚገመቱ የሕክምና ቁሳቁሶችን ድጋፍ አደረገ።

ድጋፉ ለከፍተኛ የጽኑ ህሙማን ክፍል የሚያገለግሉ የመተንፈሻ ማሽን፣ የልብ ምት እና የተለያዩ የሰውነት ክፍሎችን መለካት የሚያስችል ማሽን እና የፅኑ ህሙማን ክፍል አልጋዎች መሆናቸውን የፌደራል ፖሊስ መረጃ አመላክቷል፡፡