Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

አቶ ሽመልስ አብዲሳ የአርሶ አደሩን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እየተሠራ መሆኑን ገለጹ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 12፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የአርሶ አደሩን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ማረጋገጥ የሚያስችሉ የግብርና ኢንሼቲቮች እየተተገበሩ መሆኑን የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር ሽመልስ አብዲሳ ገለጹ፡፡

አቶ ሽመልስ በኢሉአባቦር ዞን ሀሉ ወረዳ በኩታ ገጠም በመልማት ላይ ያሉ የሻይ ቅጠል እና ሌሎች ልማቶችን  ጎብኝተዋል፡፡

በዚሁ ወቅትም በክልሉ የአርሶ አደሩን እና የሀገርን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ያረጋግጣሉ ተብለው ተስፋ ከተጣለባቸው መስኮች አንዱ የሻይ ቅጠል ልማት መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በኢሉባቦር ዞንም ሥራውን በአርሶ አደሮች ዘንድ ለማስፋፋት እየተሠራ መሆኑን ገልጸው÷ መንግሥት የሻይ ቅጠል ልማትን ጨምሮ የአርሶ አደሩን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ የግብርና ኢንሼቲቮችን ቀርጾ እየተገበረ ነው ብለዋል፡፡

በኢሉአባቦር ዞንም የሻይ ቅጠልን ጨምሮ ሩዝ፣ ስንዴ፣ ማር እና የቡና ልማት ኢንሼቲቮች በግንባር ቀደምትነት እየተተገበሩ መሆኑን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

በአሁኑ ወቅት በዞኑ በ2 ሺህ 475 ሔክታር ላይ የሻይ ልማት ሥራ በአርሶ አደሮች እየተከናወነ መሆኑን የዞኑ ግብርና ጽሕፈት ቤት አስታውቋል፡፡

Exit mobile version