የሀገር ውስጥ ዜና

የከተማ አስተዳደሩ የሥራ ኃላፊዎች በመርካቶ ሸማ ተራ አካባቢ የተከሰተውን የእሳት አደጋ ጉዳት ተመለከቱ

By amele Demisew

October 22, 2024

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 12፣ 2017፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሥራ ኃላፊዎች በመርካቶ ሸማ ተራ አካባቢ የተከሰተው የእሳት አደጋ በንብረት ላይ ያደረሰውን ጉዳት በስፍራው ተገኝተው ተመልክተዋል።

የብልጽግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሞገስ ባልቻ በዚህ ወቅት÷ አደጋ የደረሰበት ሕንፃ 50 በመቶ ያህሉን ከአደጋው ማትረፍ መቻሉን ገልጸዋል።

የተለያዩ የማኅበረሰብ ክፍሎች እና የፀጥታ አካላት በተቀናጀ መንገድ አደጋውን ለመቆጣጠር እና አደጋው እንዳይዛመት ያደረጉት የተቀናጀ ርብርብ የሚመሰገን መሆኑንም ገልጸዋል።

የከተማ አስተዳደሩ በተከሰተው የእሳት አደጋ የንብረት ጉዳት የደረሰባቸው ወገኖችን መልሶ ለማቋቋም በትኩረት እንደሚሠራም መግለጻቸውን የከንቲባ ጽህፈት ቤት መረጃ አመልክቷል።