አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 12፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽንና ኦቪድ ግሩፕ የፒያሳ መልሶ ማልማት አካል የሆኑ ዘመናዊ የንግድ ሞሎችንና የመኖሪያ ቤቶችን ለመገንባት የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ።
ስምምነቱን የፈረሙት የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ ረሻድ ከማል እና የኦቪድ ግሩኘ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ዮናስ ታደሰ መሆናቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
የመግባቢያ ስምምነቱ የፒያሳ መልሶ ማልማት አካል በሆነው 9 ነጥብ 5 ሄክታር መሬት ላይ አራት ግዙፍ የንግድ ሞሎችንና የመኖሪያ ቤት ግንባታን በስድስት ወር ጊዜ ውስጥ በማጠናቀቅ ማስረከብ የሚያስችል መሆኑ ተገልጿል።
ስምምነቱ የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን የንግድ ሱቆችን፣ ሞልና መዝቦልድ ሞል እንዲሁም የጣይቱ የመኖሪያ አፓርትመንት በአልሙኒየም ወርክሾፕ ቴክኖሎጂ ሰርቶ በተያዘው የጊዜ ገደብ ለማጠናቀቅ መሆኑ ተጠቅሷል።
በስምምነቱ ወቅት ኦቪድ ግሩፕ ፕሮጀክቶቹን በተያዘላቸው የጊዜ ገደብ በማጠናቀቅ ለማስረከብ ዝግጁ መሆኑን አረጋግጧል፡፡