Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

14 ነጥብ 3 ሄክታር መሬት ለሊዝ ጨረታ ቀረበ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 12፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር 14 ነጥብ 3 ሄክታር መሬት ለሊዝ ጨረታ አቀረበ፡፡

የሊዝ ጨረታው ከጥቅምት 8 እስከ 21 ቀን 2017 ዓ.ም ክፍት መደረጉን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማት አስተዳደር ቢሮ ዛሬ በሰጠው መግለጫ አስታውቋል።

መግለጫውን የሰጡት በቢሮው የለማ መሬት ማስተላለፍና የሊዝ ክትትል ዳይሬክተር ጫሊ አብርሀም÷ ከቂርቆስ ክፍለ ከተማ ውጭ በሁሉም ክፍለ ከተሞች ለጨረታው የቀረቡ መሬቶች መኖራቸውን ተናግረዋል።

ይህ ከ2016 ዓ.ም ወዲህ አራተኛው ዙር ሲሆን÷ በዚህኛው ዙር ብቻ አጠቃላይ የቀረበው 143 ሺህ 140 ካሬ ሜትር ቦታ ነው ተብሏል።

ይህም በከተማ አስተዳደሩ ታሪክ በቁጥር ከፍተኛው መሆኑ ተመላክቷል።

በአሸናፊ ሽብሩ

Exit mobile version