የሀገር ውስጥ ዜና

የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ ሊወሰዱ የሚገባቸው መፍትሔዎች ምንድን ናቸው?

By ዮሐንስ ደርበው

October 22, 2024

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 12፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ በዘየርፉ የተለያዩ መፍትሔዎችን መውሰድ እንደሚገባ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ገልጿል፡፡

ሊወሰዱ ከሚገባቸው ዋና ዋና መፍትሔዎች መካከልም ከታች የተዘረዘሩት እንደሚገኙበት የአገልግሎቱ መረጃ አመላክቷል፡፡

👉 ሰላምን ማፅናት

👉 አርሶ አደሩ እና አርብቶ አደሩ በአካባቢ ባለው የውሃ አማራጭ በመጠቀም በጥምረት የመስኖ ስራን መስራት፤

👉 የተጀመረውን የስንዴ ኢኒሼቲቭ ምርትን ክረምት ከበጋ አጠናክሮ መቀጠል፤

👉 በከተማ እና ገጠር ተግባራዊ እየሆነ ያለው የሌማት ትሩፋት ስራን አጠናክሮ መቀጠል፤

👉 ዘላቂቅ እና ዘመን ተሻጋሪ የተፈጥሮና ሰው ሰራሽ የቅድመ አደጋ መከላከል ስራን እንደየ አካባቢው መስራት፤

👉 በየጊዜው በምርምርና አዳዲስ ፖሊሲ ስራውን መደገፍና ማጠናከር፤

👉 በጉዳዩ ላይ ሰፊ የግንዛቤ ማስጨበጥ ስራን በሁሉም አማራጮች መስራት፤

👉 የስራ እድል አማራጮችን ማስፋፋትና አዳዲስ ሀሳቦችን በማመንጨት ጥቅም ላይ ማዋል፤

👉 የገበያ አማራጭ እና የቁጠባ ዘዴዎችን መዘርጋት፤

👉 ተቋማዊ ጥረት ማጠናከር፤

👉 በዘርፉ የሀገር በቀል እውቀቶችን ማዘመን እና ጥቅም ላይ ማዋል እና

👉 ለጉዳዩ ተገቢውን ምላሽ መሰጠቱን መፈተሽ መሆናቸው ተገልጿል፡፡