ስፓርት

የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ 3ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ዛሬ ምሽት ይደረጋሉ

By ዮሐንስ ደርበው

October 22, 2024

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 12፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ 3ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ዛሬ ምሽት ቀጥለው ሲደረጉ ሪያል ማድሪድ ከቦሩሲያ ዶርትሙንድ የሚያደርጉት ፍልሚያ ይጠበቃል፡፡

ምሽት 1 ሠዓት ከ45 ላይ ኤሲሚላን ከቤልጂየሙ ክለብ ብሩዥ እንዲሁም የፈረንሳዩ ሞናኮ ከሰርቢያው ሬድ ስታር ቤልግሬድ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ፡፡

በሌላ የጨዋታ መርሐ-ግብር ምሽት 4 ሠዓት ላይ ሴንቲያጎ ቤርናቢዩ ላይ ሪያል ማድሪድ ከቦሩሲያ ዶርትሙንድ የሚያደርጉት ጨዋታ ተጠባቂ ነው፡፡

በተመሳሳይ ምሽት 4 ሠዓት ላይ አርሰናል ከዩክሬኑ ሻክታር ዶኔስክ፣ አስቶንቪላ ከጣሊያኑ ቦሎኛ፣ የስፔኑ ዢሮና ከስሎቫኪያው ስሎቫን ብራቲስላቫ እንዲሁም ጁቬንቱስ ከጀርመኑ ስቱትጋርት ይጫወታሉ፡፡

በተጨማሪም የፈረንሳዩ ፒኤስጂ ከደቹ ፒኤስቪ እና የኦስትሪያው ስቱርም ግራዝ ከፖርቹጋሉ ስፖርቲንግ ሊዝበን በተመሳሳይ ምሽት 4 ሠዓት ላይ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ፡፡