የሀገር ውስጥ ዜና

በኦሮሚያ ክልል 93 ቢሊየን ብር ካፒታል ላስመዘገቡ ባለሃብቶች የኢንቨስትመንት ፈቃድ ተሰጠ

By Mikias Ayele

October 21, 2024

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 11፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦሮሚያ ክልል ባለፉት ሶስት ወራት 93 ቢሊየን ብር በላይ ካፒታል ላስመዘገቡ 4 ሺህ 316 ባለሃብቶች የኢንቨስትመንት ፈቃድ መስጠቱን የክልሉ ኢንቨስትመንትና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ አስታውቋል፡፡ የቢሮው ሃላፊ አቶ አሕመድ እንድሪስ እንዳሉት÷በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያ ሩብ ዓመት ባለሃብቶች በክልሉ መዋዕለ ንዋያቸውን እንዲያፈሱ በትኩረት ተሰርቷል፡፡ በዚህ መሰረትም 93 ቢሊየን ብር በላይ ካፒታል ላስመዘገቡ 4 ሺህ 316 ባለሃብቶች በተለያዩ ዘርፎች የኢንቨስትመንት ፈቃድ መውሰዳቸውን ጠቁመዋል፡፡ ባለሃብቶች በፍጥነት ወደ ሥራ እንዲገቡ አአስፈላጊው ክትትት እየተደረገ መሆኑንም ሃላፊው ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ተናግተዋል፡፡ በፀሃይ ጉሉማ