Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ዶ/ር መቅደስ የወባ በሽታን ለመከላከል እየተከናወኑ ያሉ ተግበራት ተጠናክረው እንዲቀጥሉ አሳሰቡ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 11፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ የወባ በሽታ ሥርጭትን ለመከላከልና ለመቆጣጠር እየተከናወኑ ያሉ ተግበራት ተጠናክረው እንዲቀጥሉ አሳስበዋል፡፡

የጤና ሚኒስቴር የወባ ወረርሽኝን ለመከላከልና ለመቆጣጣር እየተካሄደ ያለውን ተግባራት አስመልክቶ ሳምንታዊ ግምገማ አካሂዷል፡፡

በበይነ መረብ በተደረገው ውይይት ዶ/ር መቅደስ÷የወባ በሽታን ለመከላከልና ለመቆጣጠር እስካሁን የተከናወኑ ተግባራት አበረታች መሆናቸውን አንስተዋል፡፡

በቀጣይ የታዩ ክፍተቶችን በማረም የወባ በሽታን ለመከላከልና ለመቆጣጠር እየተከናወኑ ያሉ ተግባራት ተጠናክረው እንዲቀጥሉ አሳስበዋል፡፡

በሕብረተሰቡ ዘንድ ግንዛቤ መፍጠር የሚያስችሉ ንቅናቄዎችን ማከናወን እንዲሁም የመድሃኒትና የግብዓት አቅርቦት ሥርጭት ላይ ተገቢ ቁጥጥር ማድረግ እንደሚገባም አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡

ባለድርሻ አካላት ትብብራቸውን የበለጠ በማጠናከር አፋጣኝና ቀልጣፋ የመከላከልና የመቆጣጠር ሥራዎች እንዲሰሩ መመሪያ መስጠታቸውንም የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡

Exit mobile version