Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የፊፋ ፕሬዚዳንት ጂያኒ ኢንፋንቲኖ አዲስ አበባ ገቡ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 11፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የዓለም አቀፉ የእግር ኳስ ማህበር (ፊፋ) ፕሬዚዳንት ጆያኒ ቪንቼንዞ ኢንፋንቲኖ አዲስ አበባ ገብተዋል፡፡

ፕሬዚዳንቱ በአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) 46ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ ላይ ለመሳተፍ  ነው ዛሬ ማምሻውን አዲስ አበባ የገቡት፡፡

ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ (ዶ/ር )፣ የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ፓትሪስ ሞትሴፔ (ዶ/ር) እና የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ኢሳያስ ጅራ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

Exit mobile version